logo

በሀገራችንአንጋፋከሚባሉትከፍተኛተቋማትተርታየሚሰለፈው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ስራ ከጀመረ 25 ዓመት ሆኖታል።በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ካሉ 5 ግቢዎች አንዱ በዓይደር ክ/ከተማ የሚገኘው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ1995 ዓ/ም ስራውን ጀመረ በአሁኑ ወቅት ለህብረተሰቡ ሰፊ የጤና አገልግሎት፣ የትምህርትና የምርምር አገልግሎቶችን በመስጠት በሀገራችን ከሚጠቀሱ የጤና ተቋማት አንዱ ነው። ሆስፒታሉ ሚያዝያ 2000 ዓ/ም በጥቂት ሰራተኞችና በእርዳታ በተገኙ የህክምና እቃዎች ስራውን ጀመረ በአሁኑ ወቅት 80 የሚሆኑ ስፔሻሊስት እና ሰብስፔሻሊስት ሀኪሞችን ጨምሮ በአጠቃላይ በኮሌጁና በሆስፒታሉ 2,500 በላይ ሰራተኞች ያሉትሲሆን4,200 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የጤናዘርፎችበማስተማር ላይ ይገኛል።

1. የመማር ማስተማር መርሀ-ግብሮች፤

 • 17የቅድመ ምረቃ መርሀ-ግብሮች፣ 2 የፒኤችዲ መርሀ-ግብሮችን እና3የሳብስፔሻሊቲመርሀ-ግብንጨምሮ 26የድህረ ምረቃ መርሀ-ግብሮችና 11 ስፔሻላይዜሽን የስልጠና መርሀ-ግብሮችን ይሰጣል
 • ከመማር ማስተማር፣ ምርምርና የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ በክልሉ በሚገኙ ከተሞች፣በተቋሙ ክሊኒኮችና ል ልዩ የህክምና አገልግሎቶች የህብረተሰብ አቀፍ ትምህርት ይሰጣል።
 • ባለፉት 2 ዓመታት በሁሉም የትምህርት ርፎችበቡድን መልክ በተቀናጀ ሁኔታ በመሰረታዊ የጤና አጠባበቅ ዙርያ የማህበረሰብ ተኮር ትምህርት በክልሉዋናዋናከተሞችአካባቢለሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎች በተለያዩ ወቅቶች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና የህክምና አገልግሎት በተግባር ከተሰሩ መካከል ናቸው።
 • የኮሌጁና የሆስፒታሉ ራእይ በ2017 ዓ/ም በአፍሪካካሉ ምርጥ 25 የህክምና፣ የመማር ማስተማርና የምርምር ተቋማት አንዱ መሆንእንዲሁም ታካሚዎች ወደ ሌላ የህክምና ተቋም ሪፈራል በማስቀረት ከጎረቤት ሀገራት በሪፈራል ለሚመጡ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነውከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላትና ከ40 በላይየውጭ ዩኒቨርሲቲዎችና ሆስፒታሎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለው ሲሆን በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ብቻ እስከአሁን ከተወካይ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር 5 ጊዜ ውይይት አካሂዷል።

   2. የምርምር አገልግሎት፤

 • በ2008 ዓ/ም ከተለያዩ የውጪ ዩኒቨርሲቲዎች ጋርበመሆን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶችና የማማከር ስራዎች ተሰርተዋል።
 • ምርምር ከተደረገባቸው ርእሶች መካከል፤ በተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ በባህላዊና ዘመናዊ የመድሃኒት አመራረትና አጠቃቀም፣ በአባቢ ጥበቃ፣በስነ-ምግብ እና ተመሳሳይ ጤና ነክ ዕክሎች ይገኙበታል።
 • በ 2007/8 ዓ/ም ብቻ በተለያዩ መድረኮችከ20 በላይ የተለያዩ ተመራማሪዎች ምርጥ የምርምር ፅሁፍ በማቅረብ ተሸላሚ ሆነዋል
 • በተጨማሪ በኮሌጁ አስተማሪዎች ከተሰሩ የማህበረሰብ አገልግሎቶች መካከል፤በትግራይ ክልል በሚገኙሆስፒታሎች ላይ የሚሰጥየድህረ ውርጃ አገልግሎት ጥራት እና ወሳኝ ነገሮች ላይ የተገኙ የምርምር ውጤቶችን

ማሰራጨት፣የነፍሰጡር ክትትል ጀምረው ያቋረጡ እናቶችንተከታትሎ በማምጣት ክትትላቸው እንዲቀጥሉ

በማድረግ ላይ ለልማት ቡድን፣ ለጤና ኤክስተንሽኖችና ሚድዋይፎች የተሰጠ ስልጠና፣የመቐለ ሰሜን ክ/ከተማ ማህበረሰብ በታለበ የእናትጡት ወተት አመጋገብ ላይ ያለውን ንቃተ‑ህሊና ማሻሻልወዘተ. ይገኙበታል

3. የማህበረሰብ አገልግሎቶች፤

ከመማር ማስተማር እና ምርምር በተጨማሪ 500 አልጋ በላይያለው ሆስፒታል በትግራይና አጎራባች ክልሎች አዋሳኝዞኖች(አፋርእናአማራ) ለሚገኝ 8 ሚልዮን ለሚጠጋ ማህበረሰብ የህክምና አገልግሎት በመስጠት በጤና ዘርፉ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል። ሆስፒታሉ በ2009 ዓ/ም ብቻ ከ 187ሺ በላይ ተመላላሽ ታካሚዎች እንዲሁም ከ 15 ሺ በላይተኝተውለሚታከሙአገልግሎት ሰጥቷል

3.1 ሆስፒታሉ ከሚሰጣቸው ህክምናዎች መካከል፤

 • የአዋቂዎች፣ የሕፃናትና ጨቅላ ሕፃናት ፅኑ ሕክምና አገልግሎት
 • የቃጠሎ ህክምና ማእከል፣
 • ዘመናዊ የኩላሊት ምርመራ እና ሕክምና/dialysis/
 • የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራና ሕክምና፣
 • ደረጃውን የጠበቀ የአልትራሳውንድ፣ ራጂ፣ ሲቲስካን እንዲሁም 3.0 ቴስላ የኤም አር አይ /ማግኔቲክ ሪዞናንስ ኢሜጂንግ/ ምርመራ፣ ደረጃውን የጠበቀ ተኝተው ለሚታከሙ፣ ተመላላሽ፣ ድንገተኛ እና የመድኃኒት መረጃ ያካተተ የፋርማሲ አገልግሎት፣
 • በሰሜኑ የሀገራችን አባቢ ፍትህ እንዲሰፍን ድርሻውን እየተወጣ የሚገኝ የአስከሬንና ህግ ነክ ምርመራዎች፤ ሆስፒታሉ ከትግራይና አባቢው ለሚመጡ በዓመት በአማካኝ 250 በላይአስከሬን ምርመራ ያደርጋል
 • ከተስፋ የማህበረሰብ አገልግሎትና መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ጋርበጋራበመሆንየአደንዛዥ እፅና አልኮል ማገገሚያ ማእከልበመክፈትከሁለትአመታትበላይበማገልገልይገኛል።
 • በደም ስር የሚደረግ የልብ ሕክምና/ካቴተራይዘሽን ላቦራቶሪ፣
 • ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስማርት ኬር(Electronic Medical Recording)፣
 • ሲጂን ማምረቻ፣
 • ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጭ ለህብረተሰቡ አማራጭ ህክምና የሚሰጥ የግል ህክምና ማእከል፣
 • ለታካሚዎች፣ ለላቦራቶሪና ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውል በግቢው የሚመነጭ የተጣራ ውሃ እና የውሃ ማጣርያ ማሺን እንዲሁም
 • በቅርቡ አገልግሎት የጀመረው የስነ‑ተዋልዶ ማእከል/ምቹ ክሊኒክ/
 • የተሟላ የላይብረሪ እና የላቦራቶሪ ማእከል ይገኙበታል

     4. በመገንባት ላይ ያሉ

 • 300 አልጋ የሚይዝ የጨረር፣ የኬሞቴራፒ እናቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎትመስጠትየሚችል የተሟላ የካንሰር ተቋም
 • በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት/ waste treatment system/በግንባታላይከሚገኙትውስጥይጠቀሳሉ።

chs g