የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ

 • በዓለምዙሪያጤንነትን፣የምግብዋስትናንናልማትንለማጥፋትዋነኛከሆኑትመካከልአንዱነው፤
 • በማንኛውምእድሜማንኛውንምሰውሊጎዳይችላል፤
 • ረዘምላለየሆስፒታልቆይታን፣ከፍተኛየሕክምናወጪንእና ሞት ማፋጠንን ያመጣል፤
 • ታዳጊ ሀገሮችን በይበልጥ ይጎዳል፡፡

በተለያየ ጊዜ በአይደር ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ACSH) እና በመቐለ ሆስፒታል የተካሄዱ ጥናቶች የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ መጠን ከፍተኛ መሆኑንያመለክታሉ:: የጥናቶቹ ውጤቶች ከሁለት ወይም ከዚያ በላይ የፀረ ተህዋስያን መድሐኒቶች የተላመዱ (Multi-Drug Resistance, MDR) ተህዋስያን በጣም ከፍተኛ መሆኑንም ያሳያሉ፡፡

ለምሳሌ በ2008 ዓ.ም በ ACSH ከቆሻሻ ውኃ ናሙናዎች (Wastewater Samples) ከተለዩትባክቴሪያዎች (Bacterial Isolates) መካከል 79.1%ቱ የአጠቃላይ MDR አሳይተዋል፡፡

 • ካልተጣራ ቆሻሻ ውኃ ከተለዩትባክቴሪያዎች መካከል

ü  Coagulase negative staphylococci (CoNS) ሙሉ በሙሉ (100%ፔኒሲሊን ጋር ተላምዷል፣

ü  ሁሉም E. coliእና Klebsiella spp. ሙሉ በሙሉ (100%) ከአምፕሲሊን ጋር ተላምደዋል፡፡

 • ከተጣራ ቆሻሻ ውኃ ከተለዩትባክቴሪያዎች መካከል

ü  ሁሉም S. aureus እና CoNS ሙሉ በሙሉ (100%) ከፔኒሲሊን ጋር ተላምደዋል፣

ü  ሁሉም E. coli, Klebsiella spp እና Citrobacter spp ሙሉ በሙሉ (100%ከአምፕሲሊን ጋር ተላምደዋል፡፡

እንዲሁም በ2007 ዓ.ም በ ACSH ከመካከለኛው ጆሮ ከተወሰደ ፈሳሽ ናሙና ከተለዩትባክቴሪያዎች መካከል 74.5%ቱ የአጠቃላይ MDR አሳይተዋል፡፡

 • (100%) ከቴቲራሳይክሊን፣ ከአምፕሲሊንና ከናይትሮፉራንቶኒን ጋር ተላምዷል፡፡

2004 ዓ.ም በ ACSH ከድህረ ቀዶ ጥገና ቁስል ኢንፌክሽኖች ከተወሰደ ናሙና ከተለዩት ባክቴሪያዎች መካከል 82.92%ቱ የአጠቃላይ MDR አሳይተዋል፡፡

በኦፕሬቲንግ ክፍል (Operation Theater) አካባቢ የተህዋስያን ብክለትን ለመለካት በ ACSH የተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው ከአየር እና ከገፅ ናሙናዎች (Air and surface samples) ከተለዩትባክቴሪያዎች መካክል 36.5%ቱ MDR አሳይተዋል፡፡

በመቐለ ሆስፒታል የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከአተት ከተወሰደ ናሙና ከተለዩት Shigella 80%ቱ የአጠቃላይ MDR ያሳዩ ሲሆን ከሰው ደም ናሙና ከተለዩትባክቴሪያዎች መካክል ደግሞ 59%ቱ የአጠቃላይ MDR አሳይተዋል፡፡ በተጨማሪም Shigella አምፕሲሊን ጋር ሙሉ በሙሉ (100%)ተላምዷል፡፡

እነዚህ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ እና MDR መጠን በጣም ከፍተኛ መሆኑን ነዉ:: በመሆኑም ሁሉም የባለድርሻ አካላት በየደረጃቸው የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የራሳቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል::

የፀረተህዋስያንመድኃኒቶችመላመድመከላከል

የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የመድኃኒት ተጠቃሚዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መንግሥት እና የግብርና ዘርፍ ትልቁን ሚና ከሚጫወቱት ባለድርሻ አካላት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር፡-

በመድኃኒት ተጠቃሚዎች በኩል

 • ከጤና ባለሙያ ትዕዛዝ ውጭ መድኃኒትን አለመውሰድ፣
 • በጤና ባለሙያ የታዘዘውን መድኃኒት በአግባቡ መጠቀም፣
 • ለሌላ ሰው መድኃኒትን አለማካፈል፣
 • ከዚህ በፊት የቀሩ (leftover) የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን አለመጠቀም እና
 • ለሁሉም ዓይነት በሽታዎች መድኃኒት እንደማያስፈልግ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

በጤና ባለሙያዎች በኩል

 • አግባብነት ያለው የጤና ባለሙያ ትዕዛዝና የመድኃኒት እደላ ልምድን መከተል፣
 • የፀረ ተህዋስያን መድኃኒት የተላመዱ በሽታዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ፣
 • የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን መላመድ እና የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለታካሚዎች ማስገንዝብ እና
 • የሙያው ሥነ ምግባርና ሕጉ በሚያዘው መሠረት ህዝቡን በአግባቡ ማገልገል አለባቸው፡፡

በመንግሥት በኩል

 • የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን መላመድ ለመከላከል የዘረጋውን ሀገር አቀፋዊ የትግበራ ዕቅድ አጠናክሮ መቀጠል፣
 • ህብረተሰቡን ለማስተማር የመረጃ መስጫ መንገዶችን (ለምሳሌ ሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣ፣ ኢንተርኔት) ማስፋፋት እና፣
 • ጥራት ያላቸውን መድኃኒቶች ማቅረብና መቆጣጠር ይገባል፡፡

በግብርና ዘርፍ በኩል

 • የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን ያለ የእንስሳት ሃኪም ትዕዛዝ ለእንስሳት አለመስጠት፣
 • የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን ለእድገት ወይም በሽታን ለመከላከል በሚል ለጤናማ እንስሳት አለመጠቀም እና፣
 • የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን አስፈላጊነት ለመቀነስ እንስሳትን መከተብ እና ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

በአጠቃላይ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላችውን አስተዋጾኦ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

በአቶ ታደለኢትቻ (MSc, Assistant Professor)

ፋርማሲ/ቤት፣ ጤ.ሳ.ኮ፣ቐለ ዩኒቨርሲቲ