ለሁሉም የመ ዩ ተመራቂዎች2011

የዘንድሮ ተመራቂዎች በሰባት የትግራይ ክልል ከተሞች ከግንቦት 5 እስከ ሰኔ 23/2011 ዓ/ም ድረስ ከተለያዩ ት/ት ክፍሎች ማለትም (ከPublic Health, Midwife, Nursing (Psychiatry, Comprehensive, Neonatal, Emergency, Neonatal Ophthalmic), Pharmacy, Laboratory, Health Informative and Physiotherapy) የተውጣጡ 322 ተመራቂ ተማሪዎቻችን በዉቕሮ፡ ዓብይ ዓዲ፡ መሆኒ፡ አላማጣ፡ ኮረም፡ ማይጨው እና መቐለ በሚገኙ ጤና ተቋማት ለቡድን ተግባር ልምምድ ተሰማርተው በርካታ ስራዎችንአከናውነዋል። በዚህም በዚህ ዐመት ተመራቂ ተማሪዎች በቡድን ተግባር ልምድ /TTP ወቅት የተከናወኑ ስራዎችን በኤግዚቢሽን መልክ ቀርቦ ሌሎች ኮሌጆችና ትምህርት ክፍሎች ተሞክሮ ለማስተላለፍ ታስበዋል። 

1. በተማሪዎቻችን ከተከናወኑ ስራዎች በከፊል  

 • ተማሪዎቻችን በሄዱባቸው ቦታዎች ሁሉ ራሳቸው ቅድሚያ ደም በመለገስና ከአካባቢው ማህበረስብ በማስተማርና በማሰተባበር 750 ከረጢት ደም እንዲለገስአድርገዋል። የአይን እና በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የHIV ምርመራ ተደጓል።
 • በየትምህርት ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር እግር ኳስ በመጫወትና በተለያዩ ምክንያት ግንኙነት በመፍጠር በጎ ተጽእኖ ፈጥረዋል። ቤት ለቤት፣ በሆቴሎች፣ ሱፐር ማርኬት፣ በጤና ተቋማትና በማረሚያ ቤት ጤና ጋር የተያያዙ ችግሮችን ፈትተዋል።
 • ተማሪዎቻችን TTP በቆዩባቸው ግዜያቶች በቡድን መስራትን፣ ተመርቀው የሚሰሩበትን ማህበረሰብና የማህበረሰቡን አኗኗርና ችግሮቹንአውቀው ችግሩን ለመፍታት የመፍትሄ ሀሳብ በማምጣትና ለዚያ የሚሆኑ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ፕሮጀክት ቀረጻን ተምረዋል። 

ለሁሉም የመ ዩተመራቂዎች2011

 ለሁሉም የመ 2011 ተመራቂዎች

2. ኤግዚቢሽን ማድርግ የታሰበበት ምክናያት

 • ከፍተኛ በጀትና በርካታ የሰው ሃይል በመመደብ ኮሌጃችን በየአመቱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለጠቅላላ የዩንቨርሰቲው ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ፣
 • ለሌሎች ኮሌጆች እና የትምህርት ክፍሎች ልምዳችንን ለማካፍል፣
 • በትጋት በጥሩ ሙያዊ ስነ ምግባር ስራቸውን ያከናወኑትን ተማሪዎችና መምህራን እውቅና እና ምስጋና ለማቅረብ፣
 • ለሚቀጥለው ዓመት የሚመጡ ተማሪዎቻችን ከዘንድሮ ተመራቂዎች ትምህርት እንዲወስዱ ለማድረግ፣
 • የተማሪ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ሊያስመርቁ ወደ መቐለ የሚመጡበት አጋጣሚን ተጠቅመን ልጆቻቸው ምን ሲማሩ፡ ምን ሲሰሩና የዩንቨርሰቲውና የኮሌጁ ማህበረሰብ ለተማሪዎቹ የሚያደርገውን ለወላጆች ግንዛቤ በመስጠት ሌሎች ወላጆችም ያለስጋት ልጆቻቸውን ወደ መቐለ ዩንቨርስቲ እንዲልኩና የዩንቨርሰቲውንም ስም በተማሪዎቹም ሆነ በወላጆች በበጎ ለማስነሳት ነው።

 ለሁሉምየመ ዩ ተመራ2011

3. በእለቱ የሚከናወኑ ተግባራት

 • ማለዳ ከ12፡00-1፡30 የችግኝ ተከላ ይደርጋል
 • ከ 2፡30 -2፡40 የመግቢያ ንግግር በ ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ
 • በ 2፡40-5፡00 የሰባቱ TTP ሳይት ስራዎች በተማሪዎች ይቀርባሉ (20 ደቂቃ ለአንድ ሳይት)
 • 5፡00-5፡30 ተማሪዎቻችን ከላክንባቸው ቦታዎች ስለተማሪዎቻችን ምስክርነት ይሰጣሉ
 • 5፡30-5፡50 የታዳሚዎችን አስተያየትና ምክክር
 • 5፡50-6፡00 ጉልህ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ተማሪና መምህራን የምስክር ወረቅት መስጠት
 • 6፡00-6፡30 አላማጣ የጤና ቡድን አጭር ተውኔት
 • 6፡30-6፡35 የቡድን አhናፊውን የዋንጫ ሽልማትና መልዕክት ማስተላለፍ (ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት)

 

ለሁሉም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች መልካም የምረቃና የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው እንመኛለን።