በዚህም ጥረታቸው የአለም አቀፍ ሚደያዎች ትኩርት መሳብ የቻሉ ሲሆን ምርጥ የሲ ኤን ኤን ጀግኖች በሚል ከ10 የአለማችን ሰዎች አንዷ ለመሆን በቅተዋል። ውድድሩ እየቀጠለ ያለ ሲሆን በሙሉ ስኬት እንዲያጠናቅቁ ድምፃችን ልንሰጣቸው ይገባል።

https://edition.cnn.com/…/cnn-heroes-top-ten-2019/index.html

1 ስልጠና ኣብ ዙርያ እንታይነትን ምክልኻልን መንቀሊ ሕማም ልቢ ሩማቲክ

ካብ ኩለን ጣብያታት ጥዕና ክ/ተማታት  መቐለ  ንዝተውፃፅኡ  ጥሙር  ጥዕና  ሰራሕተኛታት  ኣብ ዙርያ እንታይነትን ምክልኻልን መንቀሊ ሕማም ልቢ ሩማቲክ ቶንሲላይትስ ስልጠና ተዋሂቡ። ኣብቲ  እዋን  ስልጠና  ውልቀን  ከባቢን  ፅሬት ብምሕላው፣  ግንዛበ ሕብረተሰብ  ዓቢ ብምግባር፣ ካብ ጎዳእቲ ባህልታትን እምነታትን ብምዕቃብ፣ መሰረተ  ልምዓት፣  መነባብሮ  ሕ/ሰብ  ክመሓየሽ  ብምግባር ወዘተ  ዝበዝሑ ሕማማት ምክልኻል ከምዝከኣል ተገሊፁ። ብተወሳኺ ተሳተፍቲ እቲ ስልጠና ኣብ ፓኬጃት ጥሙር ጥዕና ሓደ ኣካል ገይርካ ክስራሕ ከምዝግባእ ብምሕባር ትኹረት ሂብካ ክስርሐሉ ከምዝግባእ ተዛሪቦም።

እቲ ስልጠና ኣብ ኮሌጅ ጥዕና ሳይንስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዓይደር ዝተኻየደ ኮይኑ ብዩኒቨርሲቲ መቐለ፣ ቢሮ ጥዕና ክልል ትግራይን ኢትዮፒያ ዊተን ምስዝተብሃለ ዝካየድ እዩ። ኣብ ሕማም ልቢ ሩማቲክን መንቀሊኡን ግንዛበ ንምሃብ ዓሊሙ ዝወሃብ ዘሎ እዚ ስልጠና ኣብ ቀረባ እዋን ምስ ዝምልከቶም ኣካላት ብሓባር ኣብያተ ትምህርትን ጣብያታት ጥዕናን ሓዊስካ ሕ/ሰብ ኣብ ዝእከበሎም ከባቢታት ብስፍሓት መዕበዪ ግንዛበ ትምህርቲ ከምዝወሃብ ተሓቢሩ። 

Highlights Nov 04 2019 1

2 ናይ ኢትዮጵያ ምግብን መድሓንት ቁፅፅር በዓል ስልጣን ኣብ ጎናዊ ሳዕቤናትን ተዛመድቲ ፀገማትን መድሓኒት ኣድሂቡ ኣብ ኮሌጅ ጥዕና ሳይንስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዓይደር ሰሜን ቅርንጫፍ ብዝብል ማእኸል መአከቢ ሓበሬታ ኸፊቱ። እዚ ማለት ዝኾነ ዓይነት ጎናዊ ሳዕቤን ይኹን ተዛመድቲ ፀገማት ኣብ ትካላት ጥዕና ወይ ተገልጋሊ ሕ/ሰብ እንተጋጥም በሰብ ሞያ ኣቢልካ ናብዚ ማእኸል ወይ ናብ ዋና ማእኸል አዲስ አበባ ዝተፈላለየ ሜላታት ብምጥቃም ትኽክልኛ ሓበሬታ ብእዋኑ ሪፖርት ንምግባር ከምዝሕግዝ ዝተኣመነሉ ምዃኑ ተገሊፁ። እዚ ማእኸል ኣብ ኢትዮጵያ ካብዝተጣየሹ 6 ማእኸላት ሓደ ምዃኑ ኣብ ሰሜን ኢትዮጵያ ንኸባቢ ትግራይን ዓፋርን ሓዊሱ ግልጋሎት ከምዝህብ ተገሊፁ። 

Highlights Nov 04 2019 2

3 The monthly Ayder enlightenment forum was held on the topic “Medical Research: Developing Physician-Scientists at Mekelle University”. It was conducted by the invited gust, Professor Tony Magana, Professor of Neurosurgery at college of health sciences, CHS, Ayder comprehensive specialized hospital, Mekelle University.

He shared his insights and experience in Medical research to the audience. In his talk, Prof. Tony has discussed the importance and approaches for developing physician-scientists at Mekelle University and other medical schools in Ethiopia. Prof. Tony has participated in the first major prospective study of neural tubal defects in Ethiopia over the past four years. This research has been conducted by a multidisciplinary research team and Prof. Tony has played a leading role.

There was a hot discussion, questions and comments have been raised and shared among the audience. The forum was chaired by Dr. Abraha Hailu a senior internist and cardiologist at the CHS and one of the few medical doctors who are engaged in clinical research and a rising physician-scientist.Highlights Nov 04 2019 3 2

4 የዋሽንግተን እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ግንኙነት

በቅርቡ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በሴንት ልዊስ እና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ መካከል የተደረገው ስምምነት ወደፊት በሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች እና በአፍሪካ መካከል በመማር ማስተማር እና በምርምር ላይ ጠንካራ ትብብር ይፈጥራል ተባለ።

ይህ ስምምነት እዚህ እንዲደርስ በዋሽንግተን ሴንት ልዊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ልዊስ ዎል ለ10 ዓመታት ያህል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር እና በየዓመቱ የዋሽንግተን እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች የጤና ዎርክሾፕ በማካሄድ እንዲሁም በትግራይና አካባቢው በተማሪዎች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ/resuable sanitary pads/ ድጋፍ የሚያደርግ ‘ዲግኒቲ ፕሮጀክት’ የተሰኘ የትብብር ፕሮጄክት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አመርቂ ስራዎች ሰርቷል።

በአፍሪካ አህጉር ከጋና ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ እና ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ከጤና ትምህርት ባሻገር በስነ-ጥበብ፣ ቋንቋ፣ ሕግ እና ምህንድስናን ጨምሮ ትኩረት በሚሹ መስኮች ለማስፋፋት እንዲሁም የሰራተኛ ግንኙነቶችን ማጠንከር ላይ ለመስራት የታሰበ ስምምነት መሆኑን ተገልጸዋል። ስለሆነም በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ እና በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የትብብር ግንኙነቶች፣ የምርምር፣ የትምህርት እና የፈጠራ ግንኙነቶችን ከአህጉሪቱ ጋር ለማድረግ እና ለማጠናከሪያ ያግዛል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲያችን እያካሄዳቸው ያሉ በተለይ የውጭ ትብብር ስራዎች የሚደነቅ እና የዩኒቨርሲቲው ዓላማ ለማሳካት የራሱ አስተዋጽኦ እያበረከተ ሲሆን የሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን ግልጽ ነው።

https://source.wustl.edu/…/washington-university-deepens-t…/

5 መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ከነባር ተማሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ተማሪዎቹ በመማር ማስተማር ሂደቱ ይስተዋላሉ ያሏቸውን በምግብ ቤት፣ የመጠጥ ውሃ መቆራረጥ፣ የመማሪያ ክፍልና የመዝናኛ እጥረት፣ በሬጅስትራና ሌሎች ነጥቦች በማንሳት እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል። በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካደሚክ እና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐየሎም ከበደ በተማሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል። አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች ከኮሌጁ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የሚፈቱ መሆናቸውን ጠቅሰው የተወሰኑትን ግን በዩኒቨርሲቲው እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ምላሽ የሚሹ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ኮሌጁ የ2011 ዓ/ም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስራ አፈጻጸም በተመለከተ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

Highlights Nov 04 2019 5 2

ሪፖርቱ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ማለትም በኮሌጅ፣ በሆስፒታል እንዲሁም በአስተዳደር መልኩ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎች፣ ድክመቶች እና ያጋጠሙ እንቅፋቶች ተከፍሎ በዝርዝር ከሁሉም የስራ ክፍሎች ተወካዮች በተገኙበት ቀርበዋል። በቀረበው ሪፖርት ተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሰንዝረዋል።

በመጨረሻም የጤና  ሳይንስ  ኮሌጅ  እና  ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ የተሰሩ መልካም ስራዎች እንዳሉ ሆነው በታዩ ክፍተቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ሁሉም ሰራተኛ እና ባለድርሻ አካላት ተባብረን በመስራት ችግሮቹን መፍታት  ይገባናል ብለዋል። Highlights Nov 04 2019 5

 6 ዓለም አቀፍ የአንስቴዥያ ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአንስቴዥያ ተማሪዎች ህብረት ከኮሌጁ ጋር በመተባበር የፓነል ውይይት፣ ኤግዚቭሽን እና ደም ልገሳ ዝግጅቶችን በማካሄድ በዓይደር ግቢ ተከበረ። 

Highlights Nov 04 2019 6

በ2012 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ ተማሪዎች የሚመለከት መረጃ

በ2012 የትምህርት ዘመን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲያችን የሚመጡበት ቀን በዩኒቨርስትያችን ድረገፅ፣ በፌስቡክ እና ትዊተር እንዲሁም በሬድዮ፣ ቴሌቪዥን እና በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ (www.mu.edu.et) በቅርቡ እስከምናሳውቃቸው ድረስ በትእግስት እንዲጠብቁን ለመግለፅ እንወዳለን። የሬጅስትራር ዳ/ጽ/ቤት

1 ዓለም አቀፍ የልብ ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ትግራል ልብ ማህበር በመተባበር የተከበረው ይህ በዓል ከመስከረም 28/2012 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የደም ልገሳ፣ የደም ግፊት እና የስኳር መጠን ምርመራ፣ እንዲሁም የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ ተከብሯል። በዚህም 50 ከረጢት ደም እና ለ 230 ሰዎች የስኳር እና ደም ግፊት ምርመራ ተደርጓል። በዛሬው ቀንም ለበዓሉ ማድመቂያ ከኮሌጁ ተማሪዎች እና ከሪምና ሆስፒታል የእግር ኳስ የወዳጅነት ጨዋታ በማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቅቀዋል። ዓለም አቀፍ የልብ ቀን ልቤ ልብህ/ሽ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል። 

ዩኒቨርስቲያችን የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ቅበላ ጥቅምት 14-16 2012ዓ/ መሆኑን እየገለፅን፣ ከሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ለሚመጡ ውድ ተማሪዎቻችን በፍቅር ለመቀበል ዝግጅታችን ጨርሰናል።

ወደ መቐለ በምትመጡበት ግዜ ከመናሃሪያዋች እና ከአሉላ አባነጋ ኤርፓርት አውቶብሶቻችን ተማሪዎችን ወደ ግቢዎች ያደርሳሉ!

ወደ መቐለ ከመምጣታችሁ በፊት ሁሉም ተማሪ ከዛሬ ጀምሮ

  • ወደ ድረገፃችንwww.mu.edu.et በመግባት eStudent የሚል ማስፈንጠርያ ክሊክ ማድረግ፣
  • eStudent ድረገፅ Apply Here በሚል ቅፅ የ12ኛ መልቀቅያ ፈተና የምዝገባ ቁጥር (Registration number) በማስገባት፣ ሲስተሙ በሚሰጣችሁ መመርያ መሰረት እንድትመዘገቡ እንሳሳስባለን፡፡

ማሳሰብያ፡  

  • በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር በተዘጋጀው ቅፅ መሰረት በተማሪ፣ በወላጅ እና በወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ የተፈረመ ውል በመያዝ እንድትመጡ፣
  • አምና በ አንደኛ እና ሁለተኛ ሰሚስተር በተለያየ ምክንያት ትምህርታችሁን ያቋረጣችሁ ነገርግን የመልሶ ቅበላ (ሪአድሚሽን) ተቀባይነት ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከአዲስ ተማሪዎች ጋር ወደ ግቢ እንድትገቡ እናሳስባለን እንዲሁም
  • ከተገለጸው ጊዜ ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በሰላም ኑልን!

We Really Care!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ