ረቡዕ ህዳር 19/2011 ዓ/ም ከዘጠኝ ክልሎች የተውጣጡ ሴት አመባሳደሮች(እናቶች) በወቅታዊ የሀገር ጉዳይ ምክንያት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ ከዩኒቨርሲቲው አማራሮች ፣ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት በማግኘት በቅርብ ጊዚያት በሚታዩት የሰላም ችግሮች ላይ ተወያይተዋል ፡፡

46987287 1804064949719006 4168075291853324288 n

selam 1 

የሰላም ልኡካኑ እንዳሉት ይህ የሰላም ጥሪ ሀገራችን ላይ እየተዩ ያሉት አላስፈላጊ ሁከቶችና ብጥብጦችን ለመቅረፍና በሃገሪቷ ሰላም ለማስፈን እዲሁም ተማሪዎች በሰላም ትምህርታቸው በመከታተል ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ለማገልገል እንዲችሉ ነው፡፡ በማለት አክለውም እኛ ሴቶች (እናቶች) ልጆቻችን በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ አለብን ፤የእናት ለቅሶ መቆም አለበት ፤ በብሄር ፣በዘር እና በሃይማኖት የሚለያየንን ከጎን በማድረግ በኢትዮጵያዊነታችን አንድ መሆን አለብን ፤ ሁላችንም ስለሰላም ፣ ስለፍቅር ፣ስለአንድነት ማሰብና መፀላይ አለብን ብለዋል፡፡ በተጨማሪም መምህራኖች ተማሪዎችን እንደአስተማሪ ብቻ ሳይኑ የወላጅን ፍቅር እንዲጡልን ኢትዮጵያውያን እናቶችን ወክለን የሰላም መልእክት ለማስተላለፍ እንዲሁም እኛ አንግበነው የመጣነው የሰላም ጥሪ ዩኒቨርስቲው ሆነ ተማሪው በአደራ ተቀብሎ ቃል እንዲገባልንም ጭምር ነው ብለዋል፡፡

46827189 567696120319801 3739387768451629056 n

selam 3

የመቐለ ዩኒቨርስቲ የድጋፍ ሰጪ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ እጅጉ በበኩላቸው ለሰላም ልኡካኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው ካስተላለፉ በኋላ መቐለ ዩኒቨርስቲ የሰላም ዩኒቨርስቲ እንደሆነ እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የተማሪዎች አደረጃጀቶች ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በመስራት ላይ እንዳሉ በመግለፅ ከዚህ ጋር በማያያዝ ልኡካኑ የመጡበት ዓላማ የዩኒቨርሲቲው እንደሚደግፈው እና በማንኛውም መንገድ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እንደሚሰራ ለልኡካኑ በየዩኒቨርሲቲው ስም ቃል ገብተዋል፡፡

46823852 784274805246138 7122543982936064000 n

selam 2

 ተማሪ ገ/ሃወርያ ታምራት የመቐለ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት ም/ሬዝዳንት በበኩላቸው ተማሪዎችን ከመቀበል ጀምሮ ጥሩ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ ከተማሪው ሚነሱት ጥያቄዎችም በተገቢወ መንገድ እየተፈቱ መሆናቸውን ገልፃል፡፡

ይህ የሰላም ጥሪ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተጀመረ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ቀጣይ እንደሚሆን ልኡካኑ ገልፀዋል፡፡