​21/02/2013

መቐለ ዩኒቨርስቲ ፍላጎት እና ብቃት ያላቸውን አመልካቾች  በሙሉ ለፕሬዚዳንትነት ቦታ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል ፡፡

መስፈርቶች:

ሀ. የትምህርትደረጃ: ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ /ማስትሬት/  ከረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ ጋር

ለ. የስራልምድ: በከፍተኛ ትምህርት ወይም ከዚህ ውጭ ባለመስከ (በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በመሪነት ደረጃ ያገለገለ/ች) በከፍተኛ አመራርነት የተረጋገጠ የስራ ልምድ ያለው/ያላት፡፡ በመማር ማስተማርና በምርምር ቢያንስ ስድስት ዓመት እንዲሁም በከፍተኛ የሥራ አመራር የሦስት ዓመታት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፡፡

ሐ. የስትራቴጂክ እቅድን ማዘጋጀት እና ማቅረብ (ከ 10 ገጾች ያልበለጠ)

  • ዕጩ ተወዳዳሪ የተማሪ ቅበላን በብቃት ለመምራት ያላቸው አቅም፣ ኣዲስ ሃሳቦችን ለማፍለቅና ለተማሪዎች ተግባራዊ በሆነ መንገድ ለማድረስ ያላቸው ትጋት፣የትንተናና ስትራትጂካዊ ክህሎቶች፣ስለከፍተኛ ትምህርት ስራ ያላቸው ግዛቤ
  • ከመንግስት እና በጎአድራጊዎች ገቢ ለማስገኘት ያላቸው ችለታ፣ክህሎት እና ልምድ ከአሉምኒ ጋር ያላቸው ጥሩ ግኑኝነት፣ የህዝብ ከበሬታ በቀጣይነት ሊሰሯቸው ያሰቧቸው ዕቅዶች
  • ለትምህርት ልህቀትና ለአካዳሚክ ነፃነት ማሻሻል ያላቸው ቁርጠኝነት
  • በዝግጅት አቀራረብ ያላቸው ጥሩ ተናጋሪነት ሙሉነት እና ግልፅነት
  • በአመራር ክህሎት እና ብቃት ላይ በፓናል የሚደረግ ቃለመጠይቅ

አመልካቾች፡

ይህ ማስታወቂያ በሜዲያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ዋናውና ፎቶኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን (ከአስር ገጽ ያልበለጠ) ስትራቴጅክ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምልመላ እና ምርጫ ኮሚቴ በአካል በመገኘት በማኔጅመንት ህንፃ ክፍል ቁጥር A1-208 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥር +251 911863347 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል

Email address: ftkiros@gmail.com

እንዲሁምየዩኒቨርሲቲውንድህረገጽwww.mu.edu.etመመልከትይቻላል

የመቐለዩኒቨርሲቲየስራአመራርቦርድ