ለሁሉም በ2017 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የኣንደኛ ዓመት (Freshman)
ወደ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት የምታደርጉበት ሕዳር 19 እና 20 2017 ዓ/ም መሆኑ እያሳወቅን፡ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመምጣታችሁ በፊት የመቐለ ዩኒቨርሲl: e-student website www.mu.edu.et ከሕዳር 13/2017ዓ/ም ጀምሮ ለምዝገባ ክፍት ስለሚሆን፡ ባላችሁበት ሆናችሁ በዌብሳይቱ ገብታችሁ እንድትመዘገበ እያሳሰብን፡ በምዝገባ ወቅት የሚከተሉት ኣስፈላጊ ዶክመንቶች ስካን በማድረግ እንድትጭኑ (Upload) እንድታድርጉ እናሳውቃለን።
1. የ8ተኛ ክፍል ሰርትፍኬት
2. የ12ተኛ ክፍል ሰርትፍኬት
በመሆኑም ወደ ዩኒቨርሲቲ በምትመጡበት ወቅት የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በዋና ግቢ' እንዲሁም የሕ/ሰብ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ በዓዲ-ሓቂ ግቢ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ማሳሰብያ
1. በ2016 ዓ/ም በዩኒቨርስትያችን በረሜድያል ፕሮግራም ስትማሩ የቆያችሁና የማለፍያ ነጥብ ያገኛችሁ እላይ ለኣንደኛ ዓመት ተማሪዎች የተጠቀሰው መሰረት በበየነ መረብ (Online) ·1-ምዝግባችሁ ሕዳር 19 እና 20 2017 ዓ/ም በኣካል ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
2. 112017 ዓ/ም በረሜዲያል ፕሮግራም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ ስለምናደርግ እንድትክታተሉ እያሳወቅን፡ በረሜድያል ፕሮግራም የምድብ ዩኒቨርሲትያችሁ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያልሆነ ነገር ግን በግላችሁ ከፍላችሁ መማር የምትፈልጉ ምዝገባ ስለጀምርን በዋና ግቢ ረጅስትራር ዳይሬክቶሬት በኣካል ቀርባችሁ መመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ
ረጅስትራር ዳይሬክቶሬት

Related Articles