
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የልደት በዓልን ከተማሪዎች ጋር በድምቀት አከበሩ
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል (ገና) በዛሬው ዕለት በሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ግቢዎች በድምቀት አክብረዋል፡፡
በዓሉን ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲትያችን የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተከስተ ብርሃኑን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች (የማኔጅመንት አባላት) በግቢዎቹ በመዘዋወር ከተማሪዎች ጋር ምሳ ተጋርተዋል።

ዶ/ር ተከስተ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት፤ በዓሉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡ አክለውም በዓሉ በተማሪዎች ዘንድ እንዲህ ደምቆ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።