የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ደማቅ የምርቃት ስነ-ስርዓት!

cong 2026 2 

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ደማቅ የምርቃት ስነ-ስርዓት!
​የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዘንድሮው የምርቃት ስነ-ስርዓት ለስኬት የበቁ ተማሪዎች ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡
​ጠቅላላ ተመራቂዎች፡ 2,931
(ከነዚህም ውስጥ 849ቱ ሴት ተመራቂዎች ናቸው)
​ዝርዝር መረጃ፡
​የመጀመሪያ ዲግሪ፡ 1,864 ተመራቂዎች
​ማስተርስ ዲግሪ፡ 939 ተመራቂዎች (45 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ጨምሮ)
​ስፔሻሊቲ፡ 83 ተመራቂዎች
​ዶክትሬት ዲግሪ (PhD)፡ 45 ተመራቂዎች
​"ይህ እጅግ አስደሳች ወቅት ነው። ለተመራቂዎቻችን እና ለቤተሰቦቻችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።"
ዶ/ር ፋና ሓጎስ (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት)
​እንኳን ደስ አላችሁ! 

 

cong 2026 4

Related Articles