ዩኒቨርስትያችን ከዩኒቨርሲቲ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚደረጉ የተማሪዎች የዝውውር ጉዳይን በተመለከተ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ እየተዘዋወረ መሆኑን ተገንዝቧል።

ለሚመለከተው ሁሉ


ዩኒቨርስትያችን ከዩኒቨርሲቲ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚደረጉ የተማሪዎች የዝውውር ጉዳይን በተመለከተ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ እየተዘዋወረ መሆኑን ተገንዝቧል። እነዚህ መረጃዎች "ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከሌላ ዩኒቨርሲቲ ወደ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እናዘዋውራለን/እናቀያይራለን" በማለት የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ።
​በመሆኑም ዩኒቨርሲቲያችን ይህ መረጃ ፍፁም ትክክል አለመሆኑን በመግለጽ፣ ተማሪዎች እና የሚመለከታቸው ወገኖች ይህን በመረዳት ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ ያሳስባል።

Related Articles