
የማርሻል አርት ስፖርት ወዳጆች ሆይ. እነሆ አንድ መልካም ዜና!
06/10/2018ዓ/ም
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ ከትግራይ ዓለም አቀፍ የማርሻል አርት ኮምባቲቭ ስፖርት ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ታሪካዊ የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

በትግራይ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የማርሻል አርት ማህበራት በጋራ በመሆን የመሰረቱት ይህ "የትግራይ ዓለም አቀፍ የማርሻል አርት ኮምባቲቭ ስፖርት ማህበር" እና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ያደረጉት ይህ ስምምነት፤ በክልሉ ያለውን የማርሻል አርት ስፖርት ይበልጥ ለማሳደግ እና በጋራ ጠንክሮ ለመስራት ያለመ ነው።
ይህ የፊርማ ስነ-ስርዓት በገንፈል ሆቴል በደመቀ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን፥ ሁለቱም ተቋማት በትብብር በመስራት ስፖርቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ!
#MekelleUniversity #MartialArts #TigraySport #Mekelle #SportScience