የትምህርት ሚኒስቴር የድጋፍና2017

 የትምህርት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማናጅመንት ጋር ተወያየ።
የትምህርት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ከዛሬ ሚያዝያ 20/2017 ዓም ጀምሮ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚዘልቅ የስራ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በዚህም መሰረት ዛሬ ከ2:30 ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲያችን ማኔጅሜንት ጋር በዋና ዋና የስራ አፈፃፀም ማለትም
በቁልፍ የአፈጻጸም መለክያዎች/KPI/ ኣተገባበር፣ ተቋማዊ አገራዊ ሪፎርም አተገባበር፣ በተለይ ከዲፈረንሴሽን አንፃር፣ በዲጅታላይዜሸን፣ በአስተማሪዎችና ተማሪዎች እርካታ፣ በማህበረ ሰብ አገልግሎት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል።