
መቐለ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮለጅ የስነ _ምድር ት/ቤት አውደ ጥናት አካሄደ።
መቐለ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የሰነ_ምድር ት/ቤት "Implications of the Tigray War on Water Supply and Hydro_System:An
Insight for Reconstruction and Development." በሚል መርህ ማክሰኞ 29/2017 ዓ/ም ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎች በተገኙበት በመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ዐውደ-ጥናት ኣካሄደ ::
በዐውደ - ጥናቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር
ያደረጉ የመቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና መህበረሰብ ተሳትፎ ም/ፕ ዶ/ር እያሱ ያዘው ፣ በትግራይ የነበረው ጦርነት ምክንያት የውሃ አቅርቦት እና ስርአት ላይ ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተካሄደው ጥናት የውሃ ኣቅርቦት እና ስርዓት ወደ ነበረበት ለመመለስ ሳይንሳዊ ፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮለጅ ዲን ፕ/ር አብርሃ
ገ/ኪዳን በበኩላቸው በትግራይ በተካሄደው አውዳሚ ጦርነት የወደመ የውሃ አቅርቦት እና ስርዓት ለማሻሻል የቀረበው ዐውደ_ጥናት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ ይህ ፕሮጀክት ለቀረፁ ፣ ጥናታዊ ፁሁፍ ላቀረቡ አካላት ምስግናቸው አቅርበዋል :: በመጨረሻም በተሳታፊዎች ጥያቄና ኣስተያየት ቀርቦ መልስ ተሰጥተዋቸዋል።

