የሚገኙ ታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ የሚያስችል በጥናት ላይ የተመሠረተ የምክክር ና የውትወታ መድረክ ተጀመረ:: ​መቐለ፡ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም

​በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የነፃ ሕግ አገልግሎት ማዕከል (MULAC) ከአጋሮቹ የተባበሩት መንግሥታት
ፀረ ዕፅ እና የወንጀል ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት (UNODC) እና ከአውሮፓ ኅብረት (EU) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው " በትግራይ ክልል ተጠርጣሪዎች ና ታራሚዎች የሚገኙበት ሰብዓዊ መብትና የወንጀል ፍትሕ ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ የ ምክክር ና ውትወታ ዎርክሾፕ " (Advocacy Workshop on Human Rights and Criminal Justice Situation of Detainees in Tigray) በይፋ ተጀምሯል።


​በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የነፃ ሕግ አገልግሎት ማዕከል (MULAC) ምክትል ዳይሬክተር አይተ ዓለም አብርሃ እንደገለጹት፤ ይህ መድረክ በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ወደማረምያ ቤት ከመሄዳቸው በፈት በፓሊስ የነበራቸው ኣያያዝ እንዲሁም በማረምያ ቤት ቆይታቸው የሚደረግለቻው የሰብኣዊ መብት ጥበቃ አስመልክቶ የቀረቡ የምርምር ግኝቶችንና የሰብዓዊ መብት ክትትል ሪፖርቶችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።
​ምክትል ዳይሬክተሩ አክለውም፡
​"ይህ መድረክ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ እኛ እንደ አንድ ተቋም ማድረግ ያለብን በፓሊስ ጣብያዎች ና ማረሚያ ቤቶቻችን ያሉ ክፍተቶችን በጥናት ላይ አሰደግፈን መለየትና ያሉብንን የአቅም ውስንነቶች በጋራ በመሙላት የ ተጠርጣሪዎች ና ታራሚዎችን መብትና ደኅንነት በተሟላ መልኩ ለማስጠበቅ የበኩላችን ኣስተዋፅኦ ማድረግ ነው" ብለዋል።

ታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት ለማስ
​በዚ መደረክ፣ ከክልሉ ፍትህ ቢሮ የመጡ ዓቃብያን ህግ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ተወካዮች ና ተከላካይ ጠበቆች፣ የክልሉ ማረምያ ቤት ኮሚሽን ተወካዮች ና ኦፊሰሮች (የመቐለ ማረምያ ቤት ማእከል ጨምሮ)፣ የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ተወካዮች ና ኦፊሰሮች፣ የክልሉ ዓቃብያን ህግ ማህበር ተወካዮች፣እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ ተወካዮች ተገኝትዋል። በመሆኑም፣ በምክክር ና ውትወታ መድረኩ የተገኙት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጨምሮ በፍትህ ና ሰብኣዊ መብት ተቋሞች ና ተዋናዮች መካከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ና ታራሚዎች ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበርና የተሻለ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚያግዝ ወርክሾፕ ነው።

ታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት ለማስ
​በዛሬው ዕለት የተጀመረውና እስከ ነገ ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም (July 15–16, 2026) በሚቆየው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

 

Related Articles