መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለአርሶ አደሮች የ'ቁንጮ' ጤፍ ምርጥ ዘር ድጋፍ አደረገ። ​መቐለ | ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም

 Quncho teff farmers

​መቐለ ዩኒቨርሲቲ የህፀተ ዝናብ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ለ500 የእንደርታ ወረዳ አርሶ አደሮች የ**"ቁንጮ"** ጤፍ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን አስታወቀ። የዘር ስርጭቱ ዛሬ ሓምሌ 13/2018 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ተካሂዷል።
​ዩኒቨርሲቲው እንደወትረው ሁሉ አሁን ባለው ውስን በጀት ቢሆንም ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የማህበረሰብ አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
​ ከመርሃ ግብሩ የተደመጡ ዋና ዋና ነጥቦች፡

Quncho teff farmers1
​ዶ/ር ገብረሐዋርያ በሪሁ (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር)፡
​የማህበረሰብ አገልግሎት የዩኒቨርሲቲው አንዱና ዋነኛው ተልዕኮ መሆኑን ጠቅሰው፣ አርሶ አደሩን የመደገፉ ስራ በዚሁ እንደማይበቃና በቀጣይም ተመሳሳይ እገዛ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
​ተባባሪ ፕሮፌሰር አለሙ አርአያ (የህፀተ ዝናብ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ምክትል ዲን)፡
​ይህ የኮሌጁ እገዛ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ በዚህ ዙር ለአንድ አርሶ አደር 15 ኪሎ ግራም ምርጥ ዘር መሰጠቱን አብራርተዋል።
​ዶ/ር ወንድም ይግዛው (የእፅዋትና ፍራፍሬ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሀላፊ)፡
​ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ዘሩን በተገቢው መንገድ ተክለው የተሻለ ምርት እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን ሙያዊ ማብራሪያና ምክር ሰጥተዋል።

Quncho teff farmers111

Related Articles