
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የ2018 ዓ.ም ቁልፍ ተግባራት አመልካች እቅዶች አፈፃፀም ኮንትራት ውል ተፈራረመ ::
ከ 2017ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መተግበር የጀመረው በቁልፍ አፈፃፀም (KPI) ላይ የተመሰረተው የሶስትዮሽ አፈፃፀም ኮንትራት ዘንድሮም ተተግብሯል :: በዚህም መሰረት መስከረም 29/2018 ዓ.ም በትምህርት ሚንስቴር : በዩኒቨርሲቲዎችና በዩንቨርሲቲዎች አስተዳደር ቦርድ መካከል የሶስትዮሽ የፊርማ ስነ- ስርዓት ተካሂዷል::

ዛሬ መስከረም 30/2018ዓ.ም በመቐለ ዩንቨርሲቲ እና በትምህርት ሚኒስቴር መካከል በተደረገው ስምምነት በመቐለ ዩንቨርሲቲ በኩል የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ እና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነቱን ፈርመዋል::
