
መቐለ — ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ነፃ የሕግ አገልግሎት ማዕከል (MULAC) ከተባበሩት መንግሥታት ፀረ ዕፅና ወንጀል ጽሕፈት ቤት (UNODC) እና ከአውሮፓ ኅብረት (EU) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የማኅበረሰብ ፍትሕ ተደራሽነት ለማሰፋት ና ለ ማጠናከር የሚያግዝ፣ የዓቅም ግምባታ ሥልጠና መድረክ ተካሂዷል።
በመቐለ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መድረክ ላይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ፣ የማኅበረሰብ ሽማግሌዎች፣ የሕግ ረዳቶች ና የህዝብ ጉዳይ ህግ ፀሃፊዎች (Paralegals) ተሳትፈውበታል።
በመድረኩ የተገኙት
የዲን ተወካይ እና የነፃ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት መምህር ገብረአብዝጊ ወለስላሴ ፣እንዱሁም ምክትል ዲኑ መምህር ኣሳፋዉ ግደይ በመድረኩ ተገኝቶ ባስተላለፉት መልእክት ፤ ማዕከሉ የሕግ ተደራሽነትን በማስፋት፣ በአቅም ውስንነት ምክንያት የሕግ ከለላና ፍትሕ እንዳይሸራረፍ በተቻለ መጠን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ይህንን ዓላማ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ግን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።


የዓቅም ግምባታ ስልጣና የሰጡት የመቐለ ዪኒቨርስቲ መምህርና ጠበቃ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አቶ ካሕሳይ ግደይ ፣ማሕበረሰቡ ብህግ እምነት እንዲኖረው ማድረግ ና የፍትሕ ተደራሽነት ማስፋት መሰረታዊ ሰብኣዊ መብት ከመሆን ባሻገር ማሕበረሰቡ በህግ ስርዓቱ እምነት እንዲኖረው የሚያደርግ መሆኑ የገለፁ ሲሆን፣ፓራሌጋሎች ፣ረዳት የህግ ባለሞያዎች ና በኣማራጭ የግጭት ኣፈታት ዙርያ የሚሰሩ ሽማግሌዊች ና የህብረተሰብ ተወካዮች ግንዛቤያቸው ና ክህሎታቸው ለማሳደግ የሚረዳ ሰፋ ያለ የህግ ድጋፍ ተግባራዊ ትምህርት ኣቅርብዋል።
ከቀረበው ተግባራዊ የህግ ድጋፍ በመነሳት፣ተግባራዊ የሕግ ክህሎቶችን ማሳደግ፣
የማኅበረሰብ ተሳትፎን ማጠናከር፣ እና

ዘላቂ አጋርነትን መፍጠር በሚሉ ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ሰልጠኝዎች በኣራት ቦታዎች በመከፋፈል ያካየዱት የብዱን ውይይት ተከትሎ ፣ የየራሳቸው የህግ ድጋፍ ተሞክሮዎች ና በተግባር የሚያጋጥምዋቸው ተግዳሮቶች ኣካፍልዋል። ውይይቱን የመሩት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ህግ መምህር ኣቶ ኣለም ኣብርሃ፣ የተካየደው ውይይት የህግ ድጋፍ ማእከሉ ከ ፓራሌጋሎች ፣ ረዳት የህግ ባለሞያዎች ና ሽማግሌዎች በጋራ መስራት እጅግ ኣስፈላጊ መሆኑና ያላቸው ግንኙነት በማጠናከር የማህበረሰቡ የፍትህ ተደራሽነት ማስፋት የግድ መሆኑ ኣሰገንዝበዋል።

ይህ የሥልጠና ፕሮጀክት «ፍትሕ ለሁሉም ተደራሽ፣ አካታች እና በማኅበረሰብ ላይ ያማከለ እንዲሆን በጋራ መሥራት» በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በተለይም የማኅበረሰብ ሽማግሌዎችንና የሕግ ረዳቶችን አቅም በመገንባት የፍትሕ ሥርዓቱን ለማገዝ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።