sixmonth report018

በትምህርት ሚኒስቴር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የለፈው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው30/06/2018 ዓ/ም

sixmonth report018

sixmonth report018
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግማሽ ዓመት ቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። sixmonth report018  
በመድረኩም የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። ሪፖርቱ በዋናነት የሚከተሉትን ነጥቦች ዳስሷል፦
የተመዘገቡ ስኬቶች፦ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት በዩኒቨርሲቲው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት።
የሪፎርም ስራዎች፦ የሪፎርም ስራዎች በአሁኑ ወቅት የሚገኙበት ደረጃ እና ተስፋ ሰጭ ውጤቶች።
ተግዳሮቶች፦ የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ በማስፈጸም ሂደት ያጋጠሙ ዋና ዋና እንቅፋቶችና መፍትሄዎቻቸው።
ይህ መድረክ የተቋሙን ጠንካራ ጎኖች ለማጠናከር እና የታዩ ድክመቶችን በማረም በቀጣይ ግማሽ ዓመት ለተሻለ ውጤት ለመስራት እንደሚያግዝ ታምኖበታል።

#MekelleUniversity #HigherEducation #PerformanceReview #Ethiopia #EducationReform

Related Articles