የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰዉ ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸዉ ያዩዋቸዉን ተግዳሮቶች እንዲፈቱ የበኩላቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰዉ ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸዉ ያዩዋቸዉን ተግዳሮቶች እንዲፈቱ የበኩላቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

ዶር ፋና በሰዉሃብትስራ ስምሪ ቴክኖ
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ የቋሚ ኮሚቴዉ አባላት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸዉ የተመለከቷቸዉን ያልተከፈለ ዉዝፍ የሰራተኞች ደመወዝን ጨምሮ በተጨባጭ ያዩዋቸዉን ችግሮች ይፈቱ ዘንድ የበኩላቸዉን እንዲወጡ ጥሪያቸዉን አቅርቧል።

ዶር ቤቴሊሄም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰዉሃብትስራ ስምሪ ቴክኖ

ዛሬ ሚያዝያ 11/2016 ዓም በቋሚ ኮሚቴዉ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ቤቴሊሄም ላቀዉ የተመራዉ ቡድን ባቀረበዉ የማጠቃለያ ሪፖርት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በጦርነቱ ጊዜና ከጦርነቱ በኃላ የ16 ወራት ዉዝፍ ደሞዝ ሳይከፈላቸዉ ላደረጓቸዉ የምርምር፣ የማህበረሰባዊ አገልግሎት ስራዎችና ከጦርነቱ በፊት የነበረዉን የዓለማቀፋዊ ግንኙነት የመመለስ ጥረት አድናቆታቸዉን ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዉ ያሉበትን የ2013 ዓም የአገልግሎቶች ዉዝፍ ዕዳ፣ የተማሪዎች የአገልግሎት ችግሮች፣ የዓይደር ሆስፒታል የግብአት ችግሮች፣ ግንባታቸዉ ተጀምሮ ያለለቁ ግንባታዎች፣ ተሟልተዉ ባለመምጣታቸዉ አገልግሎት የማይሰጡ ማሽነሪዎች፣ የዓይደር የቆሻሻ ማስወገጃ በጀት፣ ከተማሪዎች ጋር የተያያዙ በተለየ መታየት ያለባቸዉ የመዉጫ ፈተና ጊዜ ማስተካከያዎች፣ የድህረ ጦርነት ማካካሻ በጀቶች እና የመሳሰሉ ችግሮች እንዲፈቱ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመነጋገር የበኩላቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል።
በመጨረሻም መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከነበረበት በተሻለ መልኩ መልሶ እንዲገነባ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘዉ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰዉሃብትስራ ስምሪ ቴክኖ 1