መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ እና ጩራ አቦጊዳ የኪነጥበብ ማእከል ጋር በመተባበር ለሶስት ቀናት የሚቆይ ወጣቶችና የሰላም ግምባታ ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነዉ።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ እና ጩራ አቦጊዳ የኪነጥበብ ማእከል ጋር በመተባበር ለሶስት ቀናት የሚቆይ ወጣቶችና የሰላም ግምባታ ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነዉ።
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምትኩ ሃይለ አዳራሽ እየተካሄደ ባለዉ ኮንፈረስ ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ የሚኖራቸዉ ሚና፣ ተሳትፎ፣ ዉክልናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የምርምር ስራዎች ቀርበዋል።
በኮንፈረንሱ ከ 500 በላይ ከትግራይ ኣብዛኛዎቹ ወረዳዎች የተወከሉ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
 
መ ዩ ኪነጥበብ መናእሰይን ህንፀት ሰላም
በኮንፈረንሱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና ማሕበረሰባዊ ተሳትፎ ምክትል ፕረዚደንት ዶ.ር እያሱ ያዘዉ እና የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ወጣቶች ሰላምን በመፍጠር፣ እንድታብብ በማድረግና ለሁሉም በማዳረስ ረገድ ወደር የሌለዉ ሚናቸዉን እንዲወጡ ተማፅነዋል።