ላለፉት ሁለት ቀናት በመቐለ ፕላኔት ሆቴል ሲካሄድ የነበረው አገር አቀፍ የሰላም ፍትህና ዴሞክራታይዜሽን ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ ።

በኮንፈረንሱ የታደሙት ጥናት አቅራቢዎችም የተሳካ የሰላምና የፍትህ ሂደት እንዲኖር ሁሉም አካላት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ኣቅርበዋል።

neima nat con 9 10
ከጂግጂጋ ዩኒቨርስቲ የመጡ የህግ መምህርት ኒኢማ ኣብራር በሰላም ግንባታ ፖሊሲዎች፥ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በኢትዮጵያ እየታዩ ስላሉ የሰላም ችግሮች ሲገልጹ በኢትዮጵያ መንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች ቢኖሩም አሁንም ተደጋጋሚና ከፍተኛ አለመረጋጋት ይስተዋላል በማለት ለዚህም በኦሮሚያ፣በትግራይ፣በቤንሻንጉል ና በአማራ ክልሎች እያጋጠሙ ያሉት የሰላም ችግሮች በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

Befkadu nat conf law 9 10

በፍቃዱ ደርቤ ሌላ ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የታደሙ የህግ መምህር ሲሆኑ በሰላም እና ፍትህ መካከል ስላለው የረጅም ጊዜ የጥፋት ጥላ እና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ማስፈን ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስታት በኩል የሚታዩ ፍትህና ተጠያቂነት የማስፈን ችግርች እንደነበሩ አስቀምጧል።
ከዚ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ፍለጋና ፈተናዎች፣ የሴቶች ተሳትፎ በሰላም ግንባታ ሂደት በኢትዮጵያ፣የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ላይ ያላቸው ሚናና አገር በቀል የሆኑ የግጭት አፈታት አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ ላይም ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

nat conf 9 10 final
ለሁለት ቀናት የተካሄደው ሀገር አቀፍ የሰላም ፍትህና ዴሞክራታይዜሽን ኮንፈረንስ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ህግ ትምህርትቤት ሃላፊ ዶክተር ዝበሎ ሃይለስላሴ ኮንፈረንሱ ላዘጋጁ አካላት፥ ለመቐለ ዩኒቨርስቲ ማነጅመንትና ተሳታፊዎች ምስጋናቸውን አቅርቧል።