አገር አቀፍ የ ሰላም የፍትህና ዴሞክራታይዜሽን ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል

አገር አቀፍ የ ሰላም የፍትህና ዴሞክራታይዜሽን ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል
የመቐለ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት ከፌደራል ህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ አገር አቀፍ የሰላም ፣ፍትህ ና ዲሞክራታያዜሽን ኮንፈረንስ በመቐለ ፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል ።


በኮንፈረንሱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የመቐለ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ምክትል ፕረዚደንት ዶክተር ዐብደልቃድር ከዲር ፍትህ፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ለሰው ልጅ ወሳኝ እንደሆኑ በመግለፅ በአገሪቱ እንዲስፋፉም ሁሉም ሰው የበኩሉን ኣስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፏል።

Amba Degife Bula Director nation confe law
የኮንፈረንሱ የክብር እንግዳና የፌደራል ህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ደግፌ ቡላ በበኩላቸው ሰላም ፣ፍትህ እና ዲሞክራሲ ለሰው ልጅ ከምንም በላይ ወሳኝ መሆናቸውና በቀጣይም በነዚህ ጉዳዮች ላይ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
አምባሳደሩ ከዚ በተጨማሪ ያለፈውን ረስተን ሰላምና ፍትህ እንዲረጋገጡ በጋራ በመስራት የኣገራችን እድገት እውን ማድረግ ኣለብን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፏል።
በመድረኩ የተለያዩ በሰላም ግንባታና ፍትህ መረጋገጥ ዙርያ ያተኮሩ ፅሁፎች እየቀረቡ ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል ።
ኮንፈረንሱ ነገም ቀጥሎ እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል።

national conf law 9 10