በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ!!

በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ!!

በዩኒቨርሲቲዉ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ለ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብሮች አዲስ አመልካቾች ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈው መመሪያ መሠረት የሚከተሉትን ጉዳዮች ማወቅና መተግበር የሚጠበቅባችሁ መሆኑን ከወዲሁ አጥብቀን እያሳወቅን፡-
 
 
. ሁሉም ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et መሆኑ ታዉቆ ከመስከረም 11 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በበይነ-መረብ ማመልከት የሚገባቸው መሆኑን፣
2. የመግቢያ ፈተና (GAT) የሚሰጠው ከመስከረም 21 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ የሚሰጥ መሆኑን፣
3. ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል ገብተው ሲያመለክቱ የመፈተኛ ጣቢያቸውን (ዩኒቨርሲቲ) እና ሌሎች መረጃዎችን በትክክል ተጠንቅቀው መሙላት የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
4. ተፈታኞች በGAT የመመዝገቢያ ፖርታል ገብተው ሲሞሉና ሲያመለክቱ ፈተናውን ለመውሰድ የሚያስፈልገውን ክፍያ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በቴሌ ብር አካውንት በኩል ብቻ የሚከፍሉ በመሆኑ ከወዲሁ የቴሌ ብር አካውንት መክፈት እና ዝግጁ ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
5. ተፈታኞች የፈተና ፕሮግራሞችና ተያያዥ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ- ገጽና ፖርታል www.aau.edu.et እና https://portal.aau.edu.et እንዲሁም ኦፍሻል የቴሌግራም ቻናል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን፣
6. በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ለፈተና ለመቀመጥና ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቶዋቸው ያለበትን Test Admission Ticket (TAT) ከ (http:// portal.aau.edu.et/web/applyForAdmission/TestTaker) አውርደው እና ፕሪንት አድርገው መያዝ የሚጠበቅባቸው መሆኑን፣
7. የፈተና ውጤት ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱና በመጨረሻ መልሳቸውን ሲያስገቡ ወዲያውኑ ማየት የሚችሉ መሆኑን፣
8. የማለፍያ ነጥብ የሚወሰነዉ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል መሆኑን፣
9. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (GAT) ያለፉ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲዉ ት/ት ክፍሎች የሚያዘጋጁትን የመግቢያ ፈተና እንዲወሰዱ ይደረጋል ለዚህም የፈተናዉን ቀን በዉስጥ ማሰታወቂያ ይገለፃል፡፡
10. ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ከቀድሞ ተቋሙ ከምዝገባ ወቅት ጀምሮ እስከ 60 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ማቅረብ የሚጠበቅበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡