በድህረ ጦርነት የትግራይ የትምህርት ዘርፍ ማገገምና ማነቃቃት የተመለከተ የምክክር ዐውደ-ጥናት በመቐለ ፕላኔት ሆቴል በመካሄድ ይገኛል ።

 በድህረ ጦርነት የትግራይ የትምህርት ዘርፍ ማገገምና ማነቃቃት የተመለከተ የምክክር ዐውደ-ጥናት በመቐለ ፕላኔት ሆቴል በመካሄድ ይገኛል ።

ፕሮፌሰርክንደያ ገ በድ ጦ ት ት ማገገምና
በምክክሩ የተገኙት በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር የማህበረሰብ ልማትና ሽግግር ሴክረታርያት ኃላፊ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት ጦርነቱ ከባድ ጉዳት ማድረሱን በመግለጽ ለብዙ አስርት አመታት ወደ ኋላ መልሶታል ብለዋል።
ችግሩ ለመፍታት ደግሞ የሁሉም ሰው ድርሻ ስለሆነ ሁሉም የአቅሙ እንዲያበረክት ጠይቀዋል።
ጊዝያዊ አስተዳደራቸውም ትምህርትን ማነቃቃት በቅድሚያ ከያዛቸው ጉዳዮች መሆኑ አበክረው ተናግረዋል ።
በሁለት ቀን የምክክር ኮንፈረንሱ የተለያዩ ችግሮችን የመለየት የመፍትሄ ሃሳቦች በማስቀመጥ በትምህርት ስርዐቱ እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችና መፍትሄዎቻቸው ፥ የምገባ ስርዐት ማስፋፋትና የትምህርት እንቅስቃሴው ለማነቃቃት የሚኖረው ሚና ፥በአድዋና ዓቢይ ዓዲ የመምህራን ኮሌጆችና የአጼ ዮሃንስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደረሰው ውድመትና ያስከተለው ጉዳት፥ ከጦርነት በኋላ የትግራይ መምህራንና ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታና መፍትሄዎቻቸው በስፋት ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በድህረ ጦርነት ት ት