መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ ሺ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የአገር አቀፍ ሪሜድያል ፈተና በኦንላይን እየሰጠ ነው።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ዓመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላላመጡ በተፈጥሮ ሳይንስ 710፣ በማሕበረሰባዊ ሳይንስ 410 ተማሪዎች በጠቅላላ 1120 ተማሪዎች በአገር አቀፍ የሚሰጠው የሪሜድያል ፈተና እየሰጠ ይገኛል። ዛሬ ለፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለአራት ወራት የማጠናከርያ ትምህርት የተሰጣቸው መሆኑን የዩኒቨርስቲያችን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ዓብደልቃድር ከድር ገልጸዋል።